የቻይናውን ፕሬዝዳንት የቀረፀው የእናት ምክር

17 Hrs Ago 105
የቻይናውን ፕሬዝዳንት የቀረፀው የእናት ምክር

በ12ኛው ክፍለ ዘመን በቻይና ዩ ፌይ ተብሎ የሚጠራ የአርበኞች ወታደራዊ ኮማንደር እናት በጀርባዋ "ሀገርህን በፍፁም ትጋት በጀግንነት በቁርጠኝነት አገልግል" የሚል መፈክርን የያዘ ታሪክ የአሁኗ የቻይና ፕሬዝዳንት እናት አንብበውታል።

ይህ በኮማንደሩ እናት ጀርባ ያነበረው ፅሁፍ ለአሁኗ የቻይና ፕሬዝዳንት እናት ልጆቿን  ለማሳደግ እንደ ህይወት መመሪያ ሆኖም አገልግሏል።

"እናትህ የመጀመሪያዋ ትምህርት ቤትህ ናት" የሚሉት የአሁኑ የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ በልጅነታቸው ከእናታቸው የቀሰሙት ምክር በአእምሯቸው ሁሌም እንደ ስኬት መንገድ የህይወታቸው መመሪያ አድረገው እየተገበሩ መሆናቸውን ይናገራሉ።

እ.አ.አ በ1939 የኮሚዩኒስት ፓርታ አባል በመሆን ስራቸውን የጀመሩት ፕሬዝደንት ዢ ጂንፒንግ በህይወት ዘመናቸው ውጤታማ እንዲሆኑ እናታቸው ከህፃንነታቸው ጀምሮ መሠረት ጥለዋል።

የፕሬዝዳንቱ እናት ኪ ዢን ልጆቻቸው ጠንክረው እንዲሰሩና ሁሉንም ተግባራት በጥሩ አመራር እንዲመሩ የሰጡት ምክር በልጆቻቸው አስተዳደግ ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል።

የ98 ዓመቷ እናት ትጋታቸው ፍሬ አፍርቶ ልጃቸው የሀገር መሪ በመሆን ቻይናን በዓለም ተፅዕኖ ፈጣሪ ሀገር ማድረግ ችለዋል።

ከልጅነታቸው ጀምሮ በእናታቸው የታነፁት የአሁኑ የቻይና ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ የሰው ልጆች አምራች እንዲሆኑ የቤተሰብ በተለይም የመጀመሪያ ትምህርት ቤት የሆነችው የእናት ሚና ከፍተኛ ነው ይላሉ።

በጉልምስና እድሜያቸው አንዲት የልብስ ስፌት ማሽን ከእናታቸው በስጦታ ያገኙት ፕሬዝዳንቱ፤ ማሽኑን በመጠቀም ልብስ መስፋት እንዲችሉና ፈተናዎችን እንዲጋፈጡ  እንዳስቻላቸው ይናገራሉ።

ስራህን ተግተህ በጥራት መከወን ከአባትህንና ከእናትህ የወረስከው ግዴታህ ነው በማለት እናታቸው ይሰጧቸው የነበረው ምክር አሁን ፕሬዝዳንት በመሆንም እየተገበሩት መሆኑንም ዢ ጂንፒንግ ይገልፃሉ።

ቻይናም "ሀገርህን በፍጹም ቁርጠኝነት አገልግል" በሚለው የእናት ምክር የዘራችውን  እያጨደች ትገኛለች።

በላሉ ኢታላ

 

 

 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top