ኢትዮጵያ ከሲንጋፖር ጋር በተለያዩ መስኮች ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር እንደምትሰራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለጹ።
አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፤ በኢትዮጵያ የሲንጋፖር አምባሳደር ሲቭራጃን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ኢትዮጵያ ከሲንጋፖር ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት በፖለቲካ እና ኢኮኖሚ መስኮች በተለይ በንግድ፣ኢንቨስትመንት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፍ የበለጠ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።
አምባሳደር ሲቭራጃ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የበርካታ ተቋማት መቀመጫ በመሆኗ አዲስ አበባ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴዎች የሚካሄድባት መሆኗን ገልጸዋል።
በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሲንጋፖር ያደረጉት የስራ ጉብኝት የሀገራቱን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆን ያረጋገጠ ነው ብለዋል አምባሳደሩ።
በውይይቱ ሁለቱ ሀገራት በባለብዙ ወገን የግንኙነት መድረክ ያላቸውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።