ኢትዮጵያ ከአፍሪካ መሪ የሆነችበት የ2024 አስደናቂ የቱሪዝም እድገት

1 Day Ago 120
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ መሪ የሆነችበት የ2024 አስደናቂ የቱሪዝም እድገት
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቱሪዝም ባሮሜትር መረጃ ቱሪዝም ከኮቪድ ወረርሽኝ ችግር ማገገሙን አመላክቷል።
 
ይህም በአውሮፓውያኑ 2024 ዓለም አቀፍ ቱሪዝም አስደናቂ ለውጥ የተመዘገበበት እንዲባል አስችሎታል።
 
በዓለም አቀፍ ደረጃ የታየው የቱሪዝም እድገት ማበብ ኳታርን ቀዳሚ ያደረገም ሆኗል።
 
የቱሪዝም ዘርፉ አስደናቂ ስኬት አስመዝግቧል የሚለው ይሄው መረጃ፣ የቱሪዝም ገቢ መቶ ሠላሳ ሰባት በመቶ ዕድገት አሳይቷል።
 
ይህም ከ2019 ጋር ሲነፃፀር፣ ከዓለም አቀፍ የቱሪዝም ግዙፍ ኩባንያዎች የላቀ እድገት ማለትም ኢትዮጵያ 40 በመቶ፣ ጃፓን 16 በመቶ፣ ቱርክ 14 በመቶ፣ ስፔን 13 በመቶ፣ ሳውዲ አረቢያ 69 በመቶ፣ ማልታ 29 በመቶ፣ ሞሮኮ 35 በመቶ፣ እና ዶሚኒካን ሪፐብሊክ 32 በመቶ እድገት አስመዝግበዋል።
 
ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ አስደናቂ ውጤት በማስመዝገብ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆናለች።
 
ይህ አስደናቂ እድገት በታሪክ፣ በባሕል እና በተፈጥሮ ድንቆች የበለፀገ መዳረሻ በመሆን የሀገሪቱ ተወዳጅነት እየጨመረ መምጣቱን ያሳያል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ የቱሪዝም ዘርፉን በማነቃቃትም ግንባር ቀደም መሆን ችላለች።
 
ከአንድ ሚሊዮን በላይ ጎብኚዎች በአውሮፓውያኑ 2024 የጎበኟት ኢትዮጵያ፣ በ2030 ቱሪዝም የበለጠ አስተዋፅዖ ሊያደርግ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።
 
በጌቱ ላቀው

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top