የአፍሪካ ኅብረት የሪፎም አጀንዳዎችን ውጤታማ ለማድረግ ኢትዮጵያ ያቀረበቻቸው 5 ነጥቦች ምንድናቸው?

2 Mons Ago 492
የአፍሪካ ኅብረት የሪፎም አጀንዳዎችን ውጤታማ ለማድረግ ኢትዮጵያ ያቀረበቻቸው 5 ነጥቦች ምንድናቸው?
የአፍሪካ ኅብረት አጀንዳ 2063ን ለማሳካት አህጉራዊ ተቋማትን ለማዘመን፣ ለማሻሻል እንዲሁም ለመከለስ በኬንያ ናይሮቢ ምክክር እየተደረገ ይገኛል፡፡
 
በመድረኩ እየተሳተፉ የሚገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ ባስተላለፉት መልእክት፤ ስብስባዎቻችንን አስተካክለናል፣ ኮሚሽኖችን ሪፎርም አድርገናል እንዲሁም ቁልፍ የህብረቱን ተቋማት ምክንያታዊ በሆነ መንግድ አሻሽልናል ብለዋል፡፡
 
ኅብረቱንና የኅብረቱን የአሰራር ዘዴዎችን ማሻሻል የስራ ቅልጥፍናን ለማረጋገጥ ቁልፍ መሆኑንም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡
 
የተጀመረውን የሪፎም አጀንዳ ውጤታማ ለማድረግ በ5 ነጥቦች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት፡፡
 
አካታችነትን ማረጋገጥ፡- አባል ሀገራቱን በማሳተፍ ትርጉም ያለው ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባትን መፍጠር፤ ቅድሚያ በሚሰጣቸው የሪፎርም አጀንዳዎች ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር ተገቢ መሆኑን አንስተዋል፡፡
 
የፋይናንስ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ፡- ራስን የመቻል አቅም መገንባት፣ ፈጠራ የታከለበት የፋይናንስ ዘዴዎቸን መቅረፅ፣ በሁሉም ዘርፎች አስቻይ ሁኔታ ማፍጠር፣ የግሉ ዘርፍን ማሳተፍ እንዲሁም አዳዲስ የፋይናን አማራጮችን መፍጠር ተገቢ መሆን አንስዋል፡፡
 
ለአፍሪካ ኅብረት አጀንዳዎች ቅድሚያ መስጠት፡- ለህብረቱ አጀንዳዎች ቅድሚያ በመስጠት ሪፎርም ማድረግ፣ ወሳኝ ለሆኑ ጉዳዮች ቀድሚያ በመስጠት፣ ለህብረቱ አጀንዳዎች ትኩረት መስጠትና ሐብትን በውጤታማነት መጠቀም፣ ሰፊ ጥናት በማድረግ በኅብረቱ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ መካከል ፍተሃዊ የስራ ክፍል ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡
 
ውይይቶችን ማጠናከር፡- የሪፎረም አጀንዳውን በጠንከራ የፖለቲካ ቁርጠኝነት መስራት፣ በአባል ሀገራቱ መካከል መደበኛና ኢ-መደበኛ ጥልቅ የሆነ ምክክርና ውይይት ማድረግ ሪፎርሙን ለማሳካት ቁልፍ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
 
በዓለም መድረክ በቅንጅትና በአንድነት መስራት፡- ለኅብረቱ ሪፎርም መሳካት አባል ሀገራቱ በዓለም መድረክ በቅንጅትና በአንድነት የመስራት እድላቸውን ማሳደግ ይገባል ብለዋል፡፡
 
ሪፎርሙ የጋራ ፍላጎት መሆኑን ለዓለም ማሳየት፣ ፈተናዎችን በተቀናጀ መንገድ በጋራ ማጋፈጥ፣ ለቅንጅታዊ ስራ አስተዋፅኦ ማድረግ፣ በትብብር መስራትን በማጠናከር የሪፎም አጀንዳዎችን ውጤታማ ለማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ በመድረኩ ገልፀዋል፡፡
 
በላሉ ኢታላ
 
 
 
 
 
 
 
 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top