መንግስት ዜጎች ፈጣንና ውጤታማ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂን በአግባቡ እየተገበረ ነው፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

2 Mons Ago 464
መንግስት ዜጎች ፈጣንና ውጤታማ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂን በአግባቡ እየተገበረ ነው፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
መንግስት ዜጎች ፈጣንና ውጤታማ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂን በአግባቡ እየተገበረ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ፡፡
 
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ እና ውጥኖች በሚል የተዘጋጀውን ኤግዚቢሽንና አውደ ጥናት አስጀምረዋል፡፡
 
ኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ዕድገት ዕድሎችን ለመጠቀም እና ፈተናዎቹን ለማለፍ በርካታ ጥረቶችን እያደረገች ትገኛለች ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን እየተገበረች እንደምትገኝ አስታውሰዋል።
 
የስትራቴጂው ወደ ትግበራ መግባት በርካታ አዎንታዊ ለውጦች አስገኝቷል ያሉ ሲሆን፣ ለአብነትም የሞባይል ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ17 ሚሊዮን ወደ 44 ሚሊዮን ማደጉን አንስተዋል፡፡
 
በዲጂታል ክፍያው የሚንቀሳቀሰው የገንዘብ መጠን በወረቀት ከሚንቀሳቀሰው የገንዘብ መጠን ጭማሪ ስለማሳየቱም ጠቁመዋል፡፡
 
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ መንግሥት የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ካውንስል በማቋቋም በሀገሪቱ የሚካሄዱ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስራዎች ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ የዜጎችንን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እና ፈጣን ለውጥ የሚያመጡ እንዲሆኑ የተለያዩ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱንም ገልጸዋል።
 
የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞን የበለጠ የሚያራምዱ የዲጂታል መንግስት ስትራቴጂ እና የኤሌክትሮኒክ ንግድ ስትራቴጂዎች መዘጋጀታቸውን በመጠቆም፣ በቅርቡ ፀድቀው ወደ ሥራ እንደሚገቡም ተናግረዋል፡፡
 
በአሸናፊ እንዳለ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top