26ኛው አህጉር አቀፍ የእንስሳት ጤና ጉባኤ በኢትዮጵያ ይካሄዳል

26 Days Ago 219
26ኛው አህጉር አቀፍ የእንስሳት ጤና ጉባኤ በኢትዮጵያ ይካሄዳል
26ኛው አህጉር አቀፍ የእንስሳት ጤና ጉባኤ "የእንስሳት ጤና ለምግብና ሥነ- ምግብ ዋስትና መረጋገጥ እና ለህበረተሰብ ጤና" በሚል መሪ ሀሳብ ከጥር 27 እስከ 30/2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ይካሄዳል።
 
በጉባኤው ከ54ቱም የአፍሪካ ሃገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ከ300 በላይ የሚሆኑ ተወካዮች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
 
ይህን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት በግብርና ሚኒስቴር የዓሳና እንስሳት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ በእንስሳት ሐብት ዘርፍ እያከናወነች ያለውን አበረታች ተሞክሮ ለሌሎች ለማስተዋወቅ ብሎም ከበሽታ ነፃ ቀጠናን ለመገንባት ጉባኤው እድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል።
 
በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ እንስሳትን በማምረት በዘርፉ ተወዳዳሪ ለመሆን እየተሰራ ስለመሆኑ አንስተዋል።
 
የእንስሳት ጤናን መጠበቅ ለህብረተሰብ ጤናም ያለው አስተዋፆ ከፍተኛ በመሆኑ በጉባኤው ላይ በትኩረት ውይይት ይደረግበታል ብለዋል።
 
በእንስሳት ሐብት ዘርፍ ተግዳሮት የሆነው የተዋህስያንና መድሃኒት መላመድ ችግርን መቋቋም በሚቻልበት ሁኔታም በጉባኤው የጋራ መግባባት ላይ ይደረሳል ተብሎ ይጠበቃል።
 
ለ3 ቀናት የሚካሄደው ጉባኤው የተሳካ እንዲሆን እና የሚጠበቁ ውጤቶች እንዲገኙ ኢትዮጵያ በቂ ዝግጅት ማድረጓ ተገልጿል።
 
በዓለም ይልፉ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top