አፍሪካ በለውጥ ምህዳር ውስጥ ትገኛለች ፤ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገቡ ይገኛሉ፡፡
አፍሪካውያኖች ምርቶችን በመግዛትና በመሸጥ በዓለም የገበያ ምህዳር ላይም እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
የአፍሪካ መሪዎች በቀጣይ ዓመታት የአፍሪካን ኢኮኖሚ ለማጎልበት ምን መስራት ይጠበቅባቸዋል? የሚለውን ጥያቄ በመያዝ፤ ኢቢሲ ሳይበር የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር እና የጋዜጠኝነትና ኮሚኒኬሽን መምህር ከሆኑት ከፕ/ር ብሩክ ኃይሉ ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡
በዚህ ዓመት የተደረገውን የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ መጠናቀቁን ተከትሎ አፍሪካውያን በቀጣይ የሚጠቅባቸው በርካታ የቤት ስራ እንዳሉ ምሁሩ ገልጸዋል፡፡
አፍሪካ በተፈጥሮ የታደለች አህጉር በመሆኖም አንጎላ እና ናይጄሪያ ለአሜሪካ ዘይት እያቀረቡ እንደሚገኝ ፕ/ር ብሩክ ኃይሉ ጠቅሰዋል፡፡
አይቬሪኮስት ለዓለም ማህበረሰብ ሀምሳ በመቶ የሚሆነውን የኮኮናት አቅርቦት የምታቀርብ መሆኗን ለአብነት ያነሱት ፕሮፌሰሩ፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ተፈጥሮ የሰጠው ሀብት በመኖሩ ያንን በመጠቀም ሀገራቸውን ማበልፀግ መቀጠል እንዳለባቸው አንስተዋል፡፡
ሆኖም ግን ብዙ ተግዳሮቶች ስለመኖሩ የገለፁት ምሁሩ፤ በፓን አፍሪካኒዝም መንፈስ የተለያዩ አጀንዳዎች እና እቅዶች በማድረግ ለውጥ ለማምጣት እየተሰራ ስለሆኑም ጠቅሰዋል፡፡
ለአብነት ያህል በአንዳንድ አፍሪካ ሀገራት የሚደረጉ ጉዞዎች ቪዛ አልባ በረራዎችን መሆናቸው የሚታወስ ነው፤ ይህ ደሞ አፍሪካዊ መንፈስ በማላበስ የእርስ በእርስ ውህደትን ማሳያ መሆኑን ፕ/ር ብሩክ ያነሳሉ፡፡
በዚህ ውህደት ውስጥ አፍሪካ እያጋጠማት ያሉ ችግሮች መካከል እንደ የአየር ለውጥ፣ድርቅ፣ህገወጥ ስደት፣አመጽ ተጠቃሽ ናቸው። በመሆኑም እንደ ኢትዮጵያ ግሪን ሌጋሲ ማካሄድ አስፈላጊ ስለመሆኑም ነው ባለሙያው የሚገልጹት፡፡
ብዙ አፍሪካ ሀገራት በኢኮኖሚ ቀውስ ተጠቂ ሆነዋል፤ ይህ ደግሞ ለአመጽ ይገፋፋል፤ በመሆኑም ይህ አመጽ የፖለቲካ ልዮነቶችን ይፈጥራል፤ ይህ ደግሞ የፖለቲካ ስርዓቱን ወደኋላ የሚጎትት እና ኋላቀር እሳቤዎች እንዲሰፍን ያደርጋል ፤ አፍሪካ በተፈጥሮ ሀብት የበለጸገች በመሆኗ ምዕራብያዊያኑ የተለያዩ ጫናዎች እያደረሱባት እንደሆነም ያብራራሉ፡፡
37 የአፍሪካ የመሪዎች ጉባዬ ላይ ሰፋ ያሉ ሀሳቦችን መነሳታቸው ይታወሳል፤ በመሆኑም የአፍሪካ መሪዎች በቀጣይ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እንደሚጠበቅባቸው ፕ/ር ብሩክ ኃይሉ ጠቁመዋል፡፡
በሜሮን ንብረት