ኬንያውያን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እያካሄዱ ነው

2 Yrs Ago 2835
ኬንያውያን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እያካሄዱ ነው

ኬንያውያን የ2022 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በዛሬው ዕለት እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡ በዘንድሮው የኬንያ ምርጫ ሀገራዊ ኢኮኖሚው ትልቅ ጉዳይ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል፡፡ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታን ለመተካት አራት እጩዎች በቀረቡበት በዚህ ምርጫ ከ22 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ድምጽ ለመስጠት መመዝገባቸው ነው የተገለፀው።የሀገሪቱ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ እና አሁን ላይ የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዊሊያም ሩቶ በምርጫው ዋነኛ ተፎካካሪዎች ናቸው ተብሏል። በዚህ የድምፅ አሰጣጥ ከፕሬዚዳንታዊ ምርጫው በተጨማሪ መራጮች የፓርላማ አባላትን፣ ሴናተሮችን እና የካውንቲ አስተዳደሮችን እንደሚመርጡ የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች 40 ሺህ የምርጫ ጣቢያዎች የተቋቋሙ ሲሆን ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ህዝቡ ድምፅ መስጠት ጀምሯል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top