የደቡብ ሱዳን የሽግግር ወቅት መራዘም በበጎ ጎን እንደሚያየው የኢትዮጵያ መንግስት አስታወቀ

2 Yrs Ago 2685
የደቡብ ሱዳን የሽግግር ወቅት መራዘም በበጎ ጎን እንደሚያየው የኢትዮጵያ መንግስት አስታወቀ
የሽግግር ሂደቱ ለሁለት ዓመታት መራዘም የደቡብ ሱዳናውያንን ጥቅም እስካስጠበቀ ድረስ የሚደገፍ ውሳኔ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በመግለጫውም፣ የደቡብ ሱዳን መንግስት የተጀመረውን ሰላማዊ ውይይት በተሳካ መልኩ ለማከናወን የምርጫ ግዜውን በሁለት ዓመታት ለማራዘም ውሳኔ ማሳለፉ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት እስካግባባና የደቡብ ሱዳናውያንን ጥቅም እስካስጠበቀ ድረስ ውሳኔውን በአዎንታ እንደሚመለከተው አስገንዝቧል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ውሳኔው በተጨባጭ ግምገማ ላይ የተመሰረተ ነው ብሎ እንደሚያምን አንስቷል። የኢትዮጵያ መንግስት ደቡብ ሱዳናውያን አሁን በጀመሩት መልኩ ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት ጥበብ የሚቀጥሉ ከሆነ የተቀመጠውን የሽግግር ሂደት ውጤታማ ሊያደርጉ እንደሚችሉ እምነት እንዳለውም አመልክቷል። ደቡብ ሱዳን ሰላማዊ ሽግግሩን በውጤታማ መልኩ እስክታሳካ ድረስ የኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ ልክ እንደስከዛሬው ሁሉ ከወንድም የደቡብ ሱዳን ህዝብ ጎን እንደሚቆም ገልጿል።
 
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top