የታንዛኒያ ብሄራዊ መከላከያ ኮሌጅ አባላት የኢኖቬሽንና ቴከኖሎጂ ሚኒስቴርን ጎበኙ

2 Yrs Ago 3043
የታንዛኒያ ብሄራዊ መከላከያ ኮሌጅ አባላት የኢኖቬሽንና ቴከኖሎጂ ሚኒስቴርን ጎበኙ
የተባበሩት የታንዛኒያ ሪፐብሊክ ብሄራዊ መከላከያ ኮሌጅ አባላት የኢኖቬሽንና ቴከኖሎጂ ሚኒስቴርን ጎበኙ።
በልዑካን ቡድኑ ውስጥ የዚምባብዌ፣ የናይጄሪያና የቡሩንዲ ዜጎችም የተካተቱ ሲሆን በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ስር እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ዙሪያ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
በዲጂታል ትራንፎርሜሽን፣ በባዮቴክኖሎጂ፣ በአዲሱ ቴክኖሎጂ እና ሕዋ ሳይንስ ዙሪያ ኢትዮጵያ እየሰራቻቸው ስላሉ ስራዎች ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።
የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ከአፍሪካ አጀንዳ 2063 እና ከአፍሪካ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ 2030 ጋር እንዲጣጣም ተደርጎ ስለመዘጋጁቱም ገለፃ እንደተደረገላቸው ከኢኖቬሽንና ቴከኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top