"ፋይዳ እያንዳንዱ ሰው ሊኖረው የሚገባ ወሳኝ ነገር ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

4 Hrs Ago 56
"ፋይዳ እያንዳንዱ ሰው ሊኖረው የሚገባ ወሳኝ ነገር ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እያንዳንዱ ሰው ሊኖረው የሚገባ ወሳኝ ነገር ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

ፋይዳ በአሁኑ ሰዓት የዜጎችን ማንነት ከመለየት ባለፈ የተለያዩ አገልግሎቶችን በቀላሉ ለማግኘት የሚያስችል እንደሆነም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ፓስፖርት ያላቸው በርካታ የውጭ ዜጎች አሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ "በተለይ ጎረቤቶቻችን ከኛ ባህል ቋንቋ እና አኗኗር ጋር የሚመሳሰል ዘይቤ ይዘው እዚሁ ይኖራሉ ይህን ለመለየት ፉይዳ ያለው ጥቅም የጎላ ነው" ብለዋል፡፡

ፋይዳ ለአንድ ኢትዮጵያዊ የዜግነቱ ማረጋገጫ ጭምር ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ፋይዳ በአሁኑ ሰዓት ከተለያዩ ተቋማት አገልግሎቶችን ለማግኘት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀላሉ ማንነትን የሚለይ በመሆኑ ጌዜን በመቆጥብ አገልግሎትን ለማሳለጥ በእጅጉ ያግዛል ብለዋል።

በአሁኑ ሰዓት ከ 15 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ባለቤት መሆናቸውንም አመልክተዋል፡፡

እስከ መጪው መስከረም ወር ድረስ እስከ 20 ሚሊዮን ለመድረስ እቅድ እንደተያዘም ጠቅሰዋል፡፡

በሚቀጥለው ዓመት እስከ 67 ሚሊዮን የመድረስ ዕድል ይኖረናል ሲሉም ተናግረዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

በሃብተሚካኤል ክፍሉ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top