ኢትዮጵያ የአፍሪካ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት ኮሚቴ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ስብሰባን በስኬት አስተናግዳለች - የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት

5 Hrs Ago 66
ኢትዮጵያ የአፍሪካ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት ኮሚቴ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ስብሰባን በስኬት አስተናግዳለች - የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት

የአፍሪካ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት ኮሚቴ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ስብሰባ መጠናቀቅን ተከትሎ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጄነራል ታዜር ገ/እግዚሃብሔር መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ 

ምክትል ዳይሬክተር ጄነራሉ በመግለጫቸው የቀጣናውን ሰላም ለማረጋገጥና የደህንነት ስጋቶች ቀድሞ ለመከላከል የድንበር ቁጥጥር ስርዓትን ማዘመን እንደሚገባ በስብሰባው ከስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል፡፡

የምስራቅ አፍሪካ አሁናዊ ሁኔታ በጥልቀት መገምገሙን የጠቆሙት ምክትል ዳይሬክተር ጄነራሉ፤ በሀገራት መካከል ጠንካራ የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር ተቋማት ግንባታ ላይ በትብብር ለመስራት ስለመስማማታቸውም አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ በስብሰባው ለቀጣናው ያላትን መልካም ተስፋ የሚያሳዩ ስራዎች አቅርባለች ያሉት አቶ ታዜር ያላትን የመልማት እና ደኅንነቷን የማረጋገጥ አቅም በተሞክሮነት አቅርባለችም ብለዋል፡፡

በአባል ሀገራት መካከል የመረጃ ልውውጥ ማድረግ የሚያስችል ስርዓትን ለመገንባት ውይይት ሲደረግበት በቆየው ስብሰባው ከ 30 ሀገራት በላይ የተወጣጡ ከ 150 በላይ ተሳታፊዎች ተካፍለውበታል፡፡

የስብሰባው ተሳታፊዎች ከስብሰባው ጎን ለጎን ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብን ጨምሮ በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን መጎብኘታቸውንም ምክትል ዳይሬክተር ጄነራል ታዜር ገ/እግዚሃብሔር ተናግረዋል፡፡

በአሸናፊ እንዳለ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top