በተራዘመው የ1 ዓመት የሥራ ዘመን በአማራና ትግራይ ክልል የተለየ ትኩረት ተሰጥቶ ይሠራል - የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

1 Day Ago 111
በተራዘመው የ1 ዓመት የሥራ ዘመን በአማራና ትግራይ ክልል የተለየ ትኩረት ተሰጥቶ ይሠራል - የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በተራዘመው የአንድ ዓመት የስራ ዘመን፤ በአማራ እና በትግራይ ክልል የተሳታፊ ልየታ እና ሌሎች የኮሚሽኑ ሥራዎች ላይ በትኩረት ይሰራል ሲሉ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ተናገሩ።

ኮሚሽነሩ የሶስት ዓመታት የሥራ ክንውን እና ወቅታዊ የሥራ እንቅስቃሴውን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ባለፉት ሶስት ዓመታት በ 11 ክልሎች በ 1 ሺህ 231 ወረዳዎች የተሳታፊዎች ልየታ ማድረጉን ገልፀው፤ የዕቅዱ አፈፃፀም 92.4 በመቶ ነው ብለዋል።

ኮሚሽኑ በአማራ ክልል በጎንደር፣ በባህርዳር፣ በደሴ እና በደብረብርሀን የተሳታፊ ልየታ እና የተባባሪዎች ስልጠና መጀመሩንም ገልፀዋል።

የተራዘመው አንድ ዓመትን በአግባቡ በመጠቀም ለተቀሩት ተግባራት ትኩረት ይሰጣል ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ፤ የዲያስፖራ ተሳትፎ ማሳደግም በቀጣይ በትኩረት የሚሰራበት እንደሆነ ገልጸዋል።

ባለፋት ሶስት ዓመታት ኢትዮጵያ የምትመክርበት ተቋም እና ተቋማዊ አሰራር መዘርጋት ተችሏል ያሉት ኮሚሽነሩ፤ ለተግባራዊነቱ የተባበሩትን አካላት በማመስገን አሁንም የተቀናጀ የባለድርሻ አካላት ትብብር አይለየን ብለዋል።

በትዕግስቱ ቡቼ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top