የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በክልሉ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የተቀናጀ የሃብት አጠቃቀም ሶፍትዌር ሥራን አስጀምረዋል።
ሶፍትዌሩ ሥራን ቀላል፣ ቀልጣፋ እና የተቀናጀ አድርጎ ለመምራት የሚያስችል መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ የሰው ኃይልን፣ የንብረት አሥተዳደርን እና ሌሎች ተግባራትን በቴክኖሎጂ ለማሥተዳደር እና ለመቆጣጠር ይረዳልም ተብሏል።
በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።