ኢትዮ ቴሌኮም የአምስተኛ ትውልድ 5G ኔትዎርክ ስራ መጀመር ጋር ተያይዞ የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት ለማስጀመር የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ተደርጓል።
ስምምነቱን የኢትዮ ቴለኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕዎት ታምሩ እና የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ጠሃ ቀመር ተፈራርመዋል።
የስማርት ሲቲ ፕሮጀክቱ በከተማው የሚሰጡትን አገልግሎቶች የሚያዘምን ሲሆን፣ ነዋሪው በተንቀሳቃሽ የእጅ ስልክ ካለበት ሆኖ በቂ መረጃ በማግኘት የዜግነት ግዴታውን መወጣት ያስችለዋል ተብሏል።
ከስምምነት ፊርማው በኋላም በቀጣይ ወደ ተጨባጭ ስራ ለመግባት ኢትዮ ቴለኮም ከጅማ ከተማ አስተዳደር ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ተገልጿል።
በስምምነት ፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የከተማው ነዋሪዎች ከተማውን ለማዘመን ኢትዮ ቴለኮም እያደረገ ላለው ጥረት ምስጋና አቅርበው፤ የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።