በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 365 ደረሰ

3 Yrs Ago
በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 365 ደረሰ

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3271 የላቦራቶሪ ምርመራ 14 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሦስት መቶ ስድሳ አምስት (365) ደርሷል።

ቫይረሱ በምርመራ የተኘባቸው ሰዎች 11 ወንዶች ሲሆኑ፣ እና ሦስቱ ሴቶች ናቸው። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፣ ከ9 እስከ 68 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 9 ሰዎች ከአዲስ አበባ (አንድ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያለው የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ፣ አንድ ሰው ከትግራይ ክልል የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ (መቀሌ ለይቶ ማቆያ)፣ አንድ ሰው ከኦሮሚያ ክልል (የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ)፣ ሦስት ሰዎች ከሶማሌ ክልል (ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ) የተገኙ ናቸው።

የዕለቱ ተጋላጭነትን በተመለከተ ስድስት ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ ሰባት ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው እንዲሁም አንድ ሰው የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌለው ናቸው።

በትላንትናው ዕለት አራት ተጨማሪ ሰዎች (ሦስት ከሶማሌ ክልል እና አንድ ከአፋር ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 120 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት በኮሮናቫይረስ ተይዘው በለይቶ ሕክምና ውስጥ የሚገኙ ሰዎች 238 ሲሆኑ፣ በጽኑ ሕክምና ውስጥ የሚገኝ ሰው የለም፤ እስካሁን ድረስ ለ62 ሺህ 300 ሰዎች ምርምራ መደረጉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ግብረመልስ
Top