እንደ ሕዝብ ከገባንበት አሁናዊ ፈተና በጋራ ለመዉጣት ሰላም የወል ግባችን ሊሆን ይገባል - የአማራ ክልል መንግሥት

7 Mons Ago
እንደ ሕዝብ ከገባንበት አሁናዊ ፈተና በጋራ ለመዉጣት ሰላም የወል ግባችን ሊሆን ይገባል - የአማራ ክልል መንግሥት

እንደ ሕዝብ ከገባንበት አኹናዊ ፈተና በጋራ ለመዉጣት ሰላም የወል ግባችን ሊሆን ይገባል ሲል የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ገለፀ።

የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ በክልሉ ወቅታዊ የሰላም ጉዳይ መልእክት ያስተላለፈ ሲሆን የመልእክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።

መንግስት ከትናንት የተረከባቸዉ እና አሁናዊ የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ከአመራር ለዉጥ ጀምሮ እስከ ዉስጥ አሠራር ሪፎርም በማድረግ በጊዜ የለኝም ስሜት እየሠራ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ሕዝብን ባልተገባ ፕሮፓጋንዳ በመናጥ የዉስጥ ሰላሙን የሚያናጉ አካላት በተደጋጋሚ ከድርጊታቸዉ እንዲቆጠቡ የሰላም ጥሪ ቢደረግም አሁንም በክፉ ድርጊታቸው ቀጥለዋል።

እነዚህን የሕዝብ ጥያቄዎች ሽፋን በማድረግና ችግሮቹን ለግል እና ለቡድን የፖለቲካ ፍላጎት መጠቀሚያ የሚያደርጉ አካላት የክልሉ ሕዝብን ለማያባራ የእርስ በእርስ ግጭት ከመዳረግ ዉጭ አንዳች ጠብ የሚል ለዉጥ አያመጡም።

ይሄን ያልተገባ  እንቅስቃሴ መግታትና ማረም የመንግስት የምንጊዜም ተቀዳሚ ሥራ ነው።

ሕዝባችን በተዛባ መረጃ  ሰላሙን እንዳይጠብቅ ጦር የሚሰብኩ ነገር ግን የጦር ሜዳ የማይገኙ የሞት አዋጅ ነጋሪዎች ፣የኅብረተሰብን የአንድነት ውል ለመናድ ሌት ከቀን የሚሠሩ፣ የደም ነጋዴዎችና የግጭት ጠማቂዎች ሰለባ ባለመሆን እንደሕዝብ ሰላሙን መጠበቅ ይገባዋል።

በመሆኑም የአማራ ሕዝብ መንግስታዊ ሥርአትን አበክሮ የሚያዉቅና  የሰላም መፍትሄ  የሚሻ ሕዝብ በመሆኑ ፅንፈኞችን በማረም  ሰላሙን ሊጠብቅ ይገባል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top