ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል ሀገር አቀፍ የገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ ሊካሄድ ነው

2 Mons Ago
ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል ሀገር አቀፍ የገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ ሊካሄድ ነው

ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል "ግድቤን ለማጠናቀቅ ቃሌን አድሳለሁ" በሚል መሪ ሐሳብ ሀገር አቀፍ የገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ ሊካሄድ መሆኑን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አስታወቀ።

የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ምክትል ዳይሬክተር ፍቅርተ ታምር፤ በዚሁ ጉዳይ ላይ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፣ ለአንድ ወር ለሚቆየው መርሐ-ግብሩ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

የገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄው በሁሉም አካባቢዎች ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ወር የሚዘልቅ መሆኑን ጠቁመው፣ ለስኬቱ ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣ ሲሉ ጠይቀዋል።

በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብር ከ500 እስከ 700 ሚሊየን ብር ለማሰባሰብ መታቀዱን ጠቅሰው፣ "ለግድባችን ሁለንተናዊ ድጋፋችን ይጠናከር" የሚል መልዕክታቸውንም አስተላልፈዋል።

4ኛው እና የመጨረሻው ዙር የውኃ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ በመጠናቀቁ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በድጋሚ እንኳን ደስ ያላችሁ የሚል መልዕክታቸውንም ማስተላለፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በ2016 ዓ.ም ለግድቡ ግንባታ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ለማሰባሰብ ታቅዷል። 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top