ሶማሊያ የተ.መ.ድ ልዩ መልክተኛን ከአገር አባረረች

5 Yrs Ago
ሶማሊያ የተ.መ.ድ ልዩ መልክተኛን ከአገር አባረረች

ታህሳስ 24፤ 2011 ዓ.ም

የሶማሊያ መንግስት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ መልክተኛ ኒኮላስ ሃይሶን ከአገሯ አባራለች፡፡

ሶማሊያ ልዩ መልእክተኛን ያባረረችው በአገር ውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ ገብተውብኛል በማለት ነው፡፡

የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መስሪያ ቤት ልዩ መልክተኛው የመንግስታቱ ድርጅት ጋር ካለን ስምምነት ውጭ ተንቀሳቅሰዋል፤ በሶማሊያ እንዲሰሩ አንፈልግም ብሏል፡፡

የአልሸባብ የቀድሞ አመራር በነበረውና በምርጫ እንዳይወዳደር ታግዶ የታሰረውን ሮቦው አስመልክቶ ኒኮላስ ሃይሶን ለሶማሊያ የፃፉትን ደብዳቤ ለመባረራቸው ምክንያት ነው፡፡

መልክተኛው በደብዳቤያቸው ሮቦው የታሰረበትን ህጋዊ ምክንያት መንግስት እንዲብራራላቸው መጠየቃቸው ተገልጿል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠንካራ ማእከላዊ መንግስት ለሌላት ሶማሊያ ድጋፍ ያደርግላት እንደነበር ተገልጿል፡፡   

አገሪቱ በመንግስታቱ ድርጅት ልዩ መልክተኛ ላይ የወሰደችው እርምጃ በውጭ ግንኙነቷ ላይ ጉዳት ሊኖረው እንደሚችል የዘገበው ሮይተርስ ነው፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top