በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ- ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር የተመራ ልዑካን ቡድን በ146ኛው የዓለም የፓርላማ ህብረት (IPU) ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ነው

1 Yr Ago 262
በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ- ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር የተመራ ልዑካን ቡድን በ146ኛው የዓለም የፓርላማ ህብረት (IPU) ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ነው
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ- ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር የተመራ ልዑካን ቡድን በባህሬን፣ ማናማ እየተካሄደ በሚገኘው በ146ኛው የዓለም የፓርላማ ህብረት (IPU) ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
አፈ-ጉባኤው በስብሰባው ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ሰላምና ደህንነትን ማስፈን ለዲሞክራሲ ለእድገትና ሰብዓዊ መብቶችን ለማስጠበቅ እና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል፡፡
 
ቀጣናዊ እና አሁናዊ ሁኔታዎችን በሚመለከት፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ግጭቶችና በቀጠናው በርካታ ችግሮች እንደተደቀኑበት ገልጸው፣ ይህንንም ለመፍታት ዓለም አቀፍ ጥረትና ትብብር የሚያስፈልግ መሆኑን አፈ ጉባኤው ገልጸዋል።
አፈ- ጉባኤው፣ ኢትዮጵያ የበርካታ ብዝሃ ማንነት አገር መሆኗን ገልጸው፣ በሁሉም መስክ የሚስተዋሉ ልዩነቶችን በውይይትና በንግግር ለመፍታት አገራዊ የምክክር ኮሚሽን አቋቁማ ለጠንካራ አገራዊ መንግስት ግንባታና ዘላቂ ሰላም እየሰራች መሆኑን አንስተዋል።
በኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ሰራ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆን ለዚህም በባለፉት አመታት የአረንጓዴ አሻራን በመተግበር ባለፉት አራት አመታት ከ25 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በማሳተፍ 25 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መትከሏን ፤ የአካባቢ ጥበቃ ስራ ሁለንተናዊ የኢትዮጵያ ወሳኝ ተግባር መሆኑን አለም በተሞክሮነት እንዲማርበት ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሻሻል እና ለመጨመር በልዩ ልዩ መሰኮች በርካታ የሪፎርም ስራዎች ማከናወኗን ለማሳያም የሴቶች የፓርላማ ተሳትፎ፣ ሴቶች ከወረዳ እስከ ፌደራል መንግስት ባሉ የኃላፊነት ቦታዎች ያላቸውን የፖለቲካ ውክልና በተለይም በፌደራል ሚኒስትር መስሪያቶች ሴቶችን በኃላፊነት ወደፊት መምጣት የአገራዊ ለውጡ ውጤት መሆኑን በንግግራቸው አስረድተዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top