በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ2ኛ ደረጃ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ስፖርት ልኡካን ቡድን ወደ ሀገሩ ተመልሷል

1 Yr Ago
በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ2ኛ ደረጃ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ስፖርት ልኡካን ቡድን ወደ ሀገሩ ተመልሷል
በ44ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አውስትራሊያ ባትረስት ከተማ ሰሞኑን በተካሄደው ውድድር ላይ በ2 ወርቅ፣ በ7 ብር፣ በ1 ነሃስ በድምሩ በ10 ሜዳልያዎች ከአለም ሃገራት 2ኛ ደረጃን የያዘው የኢትዮጵያ ስፖርት ልኡካን ቡድን ወደ ሀገሩ ተመልሷል፡፡
 
የስፖርት ልኡካኑ አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና ሌሎች አመራሮች አቀባበል አድርገውለታል።
ለአትሌቶቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላፉት አምባሳደር መስፍን የቡድኑ አባላት ላስመዘገቡት ድል ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ለስፖርት ልኡካን ቡድኑ ዛሬ ከረፋዱ 4:00 ላይ በስካይ ላይት ሆቴል የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት ፕሮግራም እንደሚካሄድ ከኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top