ኢቢሲ እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

5 Mons Ago
ኢቢሲ እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን /ኢቢሲ/ እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ፍስሐ ይታገሱ እና የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መሥራች ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ ተፈራርመዋል። የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ፍስሐ ይታገሱ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ "ታላቁ ሩጫ ወደ ቤቱ መመለሱ ደስ ብሎናል” ብለዋል። ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ በበኩሉ፣ “ታላቁ ሩጫ ከኢቢሲ ጋር አብሮ በመሥራቱ ደስተኛ ነን” ብሏል። በስምምነቱ መሠረት የ2015 ታላቁ ሩጫ በኢቢሲ በሁሉም ቻናሎች የሚተላለፍ ይሆናል። 
 
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ
ግብረመልስ
Top