ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በድሬዳዋ የደንበኞች የኔትወርክ አገልግሎት ሙከራ መጀመሩን አስታወቀ

2 Yrs Ago 1156
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በድሬዳዋ የደንበኞች የኔትወርክ አገልግሎት ሙከራ መጀመሩን አስታወቀ
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት በድሬዳዋ ከተማ ተከታታይ የደንበኞች የኔትወርክ አገልግሎት ሙከራ መጀመሩን አስታውቋል፡፡ ድርጅቱ በድሬዳዋ ከተማ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራው በ2G፣ 3G እና 4G ኔትወርኮች ማካሄዱን ጠቅሶ፡ ደንበኞች በ07 የሚጀምረውን የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መስመር ሲም ካርድ ማግኘት እንደሚችሉ ገልጿል፡፡
ኩባንያው በአገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎቱን ለመስጠት ከሚዘጋጅበት ጊዜ አስቀድሞ በተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች የኔትወርክ እና የአገልግሎት ጥራቱን በተጠናከረ ሁኔታ የሚፈትሽበት ሂደት መሆኑም ተገልጿል፡፡ ደንበኞች የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሲም ካርዶችን የድርጅቱ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት እንደሚችሉ ተጠቅሷል፡፡
ይህ የድሬዳዋ ከተማ የደንበኞች ሙከራ እስከ ሚያዝያ 2015 ዓ.ም ድረስ በ25 ከተሞች ከመንግሥት፣ ከንግድ ድርጅቶች፣ ከየአካባቢው ማህበረሰቦች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የሚካሄድ መሆኑም ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አስታውቋል፡፡ የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
 
 
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top