ቻይና በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ከአሜሪካ ጋር ያላትን ትብብር ማቋረጧን አስታወቀች

1 Yr Ago
ቻይና በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ከአሜሪካ ጋር ያላትን ትብብር ማቋረጧን አስታወቀች
ቻይና በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ከአሜሪካ ጋር ያላትን ትብብር ማቋረጧን እና በአፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ላይ ማዕቀብ መጣሏን አስታወቀች። ቻይና የአየር ንብረት ለውጥ እና የአደንዛዥ እፅ ተግባራትን ለመከላከል ከአሜሪካ ጋር የምታደርገውን ትብብር ማቋረጧን ነው የገለፀችው። ከዚህም በተጨማሪ በሁለቱ ሀገራዊ መካከል ከአሁን ወዲያ በወታደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደማታደርግም ጭምር ነው ቻይና ያስታወቀችው። ሰሞኑን የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ፣ ቻይና እንደ ሉአላዊ ግዛቷ በምትቆጥራት ታይዋን ጉብኝት ማድረጋቸው ለዚህ ውሳኔ መድረሱ ተገልጿል። በአፈ ጉባኤዋ ናንሲ ፔሎሲ እና ቤተሰባቸው ላይ ቤጂንግ ማዕቀብ የጣለች ሲሆን ማዕቀቡ ምን ላይ ያተኮረ እንደሆነ አልተገለፀም ሲል ቲ አር ቲ ዘግቧል። 
 
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top