የዚምባብዌ እንዲሁም የሳዖቶሜና ፒሪንሲፔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገቡ

1 Yr Ago
የዚምባብዌ እንዲሁም የሳዖቶሜና ፒሪንሲፔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገቡ

የዚምባብዌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍሬድሪክ ሻቫ እና የሳዖቶሜና ፒሪንሲፔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤዲቴ ራሞስ ቴንዡዋ በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤና በ40ኛው የህብረቱ አስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ሚኒስትሮቹ ቦሌ አየር ማረፍያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ሹም በሆኑት አምባሳደር ፈይሰል አልይ አቀባበል እንደተደረገላቸው ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የሁለቱም ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስተሮች በጉባኤው ለመሳተፍ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣታቸው ከፍተኛ ኩራትና ደስታ እንደተሰማቸው አምባሳደር ፈይሰል ተናግረዋል።

35ኛው የህብረቱ ጉባኤና 40ኛው የአስፈፃሚ ምክር ቤቱ ስብሰባ ኢትዮጵያ መልካም ገፅታዋን ለዓለም የምታሳይበት መልካም አጋጣሚ መሆኑን አምባሳደር ፈይሰል አልይ ተናግረዋል።

ግብረመልስ
Top