የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የሥራ ዘመን ለተጨማሪ 1 ዓመት ተራዘመ

2 Days Ago 78
የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የሥራ ዘመን ለተጨማሪ 1 ዓመት ተራዘመ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ባካሄደው 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔ፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሦስት ዓመት የስራ አፈፃፀምን ከገመገመ በኋላ ለተጨማሪ 1 ዓመት እንዲራዘም ወስኗል።
 
ኮሚሽኑ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሆኖ ስኬታማ ሥራዎችን ያከናወነ ቢሆንም ዋና ዋና ሥራዎች ባለመጠናቀቃቸው የሥራ ዘመኑ ለ1 ዓመት እንዲራዘም ከምክር ቤቱ አባላት ጥያቄ መቅረቡ ተገልጿል።
 
በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ታጥቀው የሚንሳቀሱ አካላትም በምክክር መድረኩ እንዲሳተፉ እና ሐሳባቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ ተነጋግረው እንዲፈቱ መንግስት ቁርጠኝነቱን ማሳየት እንዳለበትም በአባላቱ ተነስቷል።
 
የምክርቤቱ አባላት በውሳኔ ሀሳቡ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎች እና ሀሳቦች ካቀረቡ በኋላ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል።
 
በቶማስ ሀይሉ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top