የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ

1 Day Ago 129
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት በሁለተኛ ቀን ውሎው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክሮ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
ጉባዔው በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ለቀረቡ አመራሮችም ሹመት ሰጥቷል።
 
በዚሁ መሠረት አቶ ፍቅሬ አማን የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ እና የብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ አቶ ነጋ አበራ የክልሉ መንግስት ረዳት ተጠሪ፣ አቶ መንግሥቱ መኩሪያ የክልሉ ሚዲያ ኔትወርክ ሥራ አስኪያጅ ሆነው ቃለ መኃላ ፈጽመዋል።
 
ለክልል፣ ዞን፣ ከተማ አስተዳደር እና ለወረዳ ፍርድ ቤቶች 46 ዳኞች ቀርበው ሹመታቸው ጸድቋል።
 
ጉባዔው የክልሉ ፍርድ ቤቶች ሠራተኞች መተዳደሪያ ረቅቂ ደንብ እና የክልሉ መንግስት "የተርን ኦቨሪ ታክስ" አዋጅን መርምሮ አጽድቋል።
 
በሰለሞን ባረና

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top