የከተማ እና የገጠር የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ደረጃ በተከታታይ እናሳያለን:- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

1 Mon Ago 170
የከተማ እና የገጠር የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ደረጃ በተከታታይ እናሳያለን:- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት
የከተማ እና የገጠር የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ደረጃ በተከታታይ እንደሚያሳይ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
 
ጽሕፈት ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አቅጣጫ ኢትዮጵያ በኮሪደር ልማት ከተሞቿን በመቀየር ላይ እንደምትገኝ ገልጿል።
 
ይህም ሥራ እንቅስቃሴን እንደሚያሳልጥ፣የኢኮኖሚ እድልን እንደሚያሰፋ እና ለመኖሪያ ምቹ ከባቢን እንደሚፈጥር ጠቅሷል።
 
በመኪና መንገዶች፣ በእግረኛ ጎዳናዎች እና የብርሃን ግብዓት የማሳደግ ሥራዎች ላይ የፈሰሱ መዋዕለ ንዋዮች የመኖሪያ ቤቶችን ከንግድ ሥፍራዎች ያስተሳሰሩ፤ የዘመናዊ መሠረተ ልማትን ከዘላቂነት ጋር አመዛዝነው የተሠሩ መሆናቸውንም ጽሕፈት ቤቱ አብራርቷል።
 
በዚህ ተከታታይ የምስል አቅርቦት በተለያዩ ክልሎች ያሉ የከተማ እና የገጠር የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ደረጃ በተከታታይ እንደሚያሳይ ጽሕፈት ቤቱ ገልጾ፤ ሁሉም እንዲከታተሉት ጋብዟል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top