በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በትግራይ ያለው ሰላም ይፅና ሲሉ በሰላማዊ ሰልፍ ገልፀዋል::
"በፕሪቶርያ የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተግባራዊ ይደረግ" ሲሉም ነው በአዲስ አባባ ስታዲየም ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ የጠየቁት።
ከለሊት 11 ሰአት ጀምሮ ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ የሚገኙት የትግራይ ተወላጆች "የትግራይ ህዝብ ሰላም ይፈልጋል ፖለቲከኞች በሰከነ መንገድ አለመግባባታቸውን ይፍቱ" ሲሉ ተደምጠዋል።
የትግራይ ህዝብ ሰላም ይፈልጋል የትኛውንም ሰላሙን ለማፍረስ የሚደረግ ጥረት እንቃወማለን ሲሉም ገልፀዋል።