የሩሲያ መንግስት ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት ያደረገው የስንዴ ድጋፍ አለመኖሩን የኢትዮጵያ ስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት አስታወቀ

3 Hrs Ago 53
የሩሲያ መንግስት ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት ያደረገው የስንዴ ድጋፍ አለመኖሩን የኢትዮጵያ ስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት አስታወቀ
የኢትዮጵያ ስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የሩሲያ መንግስት ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት ያደረገው የስንዴ ድጋፍ አለመኖሩን ገልጾ፤ “ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት” እንደተደረገ በማስመሰል የተሳሳተ መረጃ እየተሰራጨ እንደሚገኝ መገንዘቡን አስታውቋል።
 
የራሺያ ፌደሬሽን የደቡብ ሱዳንን የእርስ በርስ ጦርነት ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ የገቡና በጋምቤላ ክልል ለተጠለሉ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች በዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) በኩል 1,632.4 ሜትሪክ ቶን የስንዴ ድጋፍ ማድረጉን አገልግሎቱ ገልጿል።
ጉዳዩን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የሰጠው ሙሉ ማብራሪያ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
 
ሀገራችን ኢትዮጵያ ከ26 ሀገራት ለመጡ ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎችን አስጠልላ ከለላና የተለያዩ መሠረታዊ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ትገኛለች፡፡
 
አገልግሎት መሥሪያ ቤታችንም በስደተኞች ስም የመጣ ማንኛውም ድጋፍ ለታለመለት ዓላማመዋሉን የመከታተልና የመቆጣጠር ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ ከዋና መሥሪያ ቤት ጀምሮ ስደተኛ ማዕከላት ድረስ የክትትልና ቁጥጥር ሥርዓት ዘርግቶ እየሠራ ይገኛል፡፡
 
በዚህም መሠረት የራሺያ ፌደሬሽን የደቡብ ሱዳንን የእርስ በርስ ጦርነት ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ የገቡና በጋምቤላ ክልል ለተጠለሉ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች በዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) በኩል 1,632.4 ሜትሪክ ቶን የስንዴ ድጋፍ አድርጓል።
 
የስደተኞች ሰብዓዊ ድጋፍ ከተለያዩ መንግስታትና ዓለም አቀፍ ተቋማት በሚደረግ ድጋፍ በዓለም የምግብ ፕሮግራም በኩል ሲከናወን ቆይቷል፤ የአሁኑ ድጋፍም የተደረገው ለተመሳሳይ ዓላማ ነው፡፡ ይህም በሩሲያ ኤምባሲ እና የዓለም የምግብ ፕሮግራም ይፋዊ መግለጫዎች በግልጽ የተመላከተ ነው።
 
ሆኖም በተለያዩ የመገናኛ ሚዲያዎች ድጋፉ “ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት” እንደተደረገ በማስመሰል የተሳሳተ መረጃ እያሰራጩ እንደሚገኙ ተገንዝበናል፡፡ በመሆኑም በተለያየ መነሻ የተሳሳተ ዘገባ ያስተላለፉና በማስተላለፍ ላይ የሚገኙ የሚዲያ ተቋማትና አካላት መረጃውን እንዲያርሙ እንጠይቃይለን፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top