የትዝታው ንጉሥ ማህሙድ አህመድ የመጨረሻ ኮንሰርት ቅዳሜ ጥር 3 በሚሊኒየም አዳራሽ በታላቅ ድምቀት ይካሄዳል።
የዚህ ታሪካዊ ኮንሰርት ብቸኛ የሚዲያ አጋር የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ሆኗል።
ኮንሰርቱ ከተካሄደ በኋላ በላቀ የኘሮዳክሽን ጥራት በኢቲቪ መዝናኛ ይቀርባል። ለታሪክም ይቀመጣል።
በቅዳሜው ታላቅ ኮንሰርት ከማህሙድ በተጨማሪ ሌሎች ዝነኛ አርቲስቶች ሙዚቃቸውን ያቀርባሉ።
በኮንሰርቱ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ የማህሙድ አድናቂዎች እና ታላላቅ የኪነጥበብ ሰዎች ይገኙበታል።
ኢቢሲ ከኮንሰርቱ አዘጋጅ ጆርካ ኤቨንት ጋር በመተባበር ታላቁን የጥበብ ትርኢት ለህዝብ ያደርሳል።