አመራሩ ለክልሉ ህዝብ ሁለንተናዊ ለውጥ መትጋት ይኖርበታል፦ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን

11 Hrs Ago 74
አመራሩ ለክልሉ ህዝብ ሁለንተናዊ ለውጥ መትጋት ይኖርበታል፦ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን
አመራሩ ለክልሉ ህዝብ ሁለንተናዊ ለውጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሊተጋ እንደሚገባው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገልጸዋል።
 
በክልሉ ላለፉት አራት ቀናት ሲካሄድ የየቆው የከፍተኛ አመራሮች ወቅታዊ የውይይት መድረክ ተጠናቋል።
 
ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በማጠቀለያ መድረኩ ላይ በመገኘት በቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ዙሪያ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።
 
አቶ አሻድሊ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ የክልሉ አመራር የዜጎችን ተጠቃሚነትን ሊያረጋግጡ በሚያስችሉ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
 
በየደረጃው የሚገኘው አመራር ለክልሉ ህዝብ ሁለንተናዊ ለውጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ መትጋት ይኖርበታል ያሉት ሲሆን፣ ህዝቡ በየደረጃው የሚያነሳቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ መፍታት እንደሚገባም አሳስበዋል።
 
በክልሉ የተገኘውን ሰላም ከማህረሰቡ ጋር በመቀናጀት በዘላቂነት በማጽናት በሁሉም ዞኖች፣ ከተማ አስተዳዳሮች እና ወረዳዎች የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች በፋጥነት ተጠናቀው ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ አመራሩ በቁርጠኝነት መምራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
 
ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ የልማት ኤኒሼቲቮች ውጤታማ እንዲሆኑ አመራሩ ግንባር ቀደም ሚናውን ሊወጣ እንደሚገባም ገልጸዋል።
 
ከመንግሥታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት ጋር ተያይዞ ህዝቡ የሚያነሳቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት ለህዝቡ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።
 
በማጠቃለያ መድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top