ሁለተኛ ቀኑን በያዘው 28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የፕሬዝደንትና ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ፌዴሬሽኑን በፕሬዝደንትነት ለመምራት 6 ዕጩዎች የቀረቡ ሲሆን፤ 26ቱ ደግሞ ለስራ አስፈጻሚነት ይፎካከራሉ፡፡
በጉባኤው ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚነት እንድትቀጥል የቀረበው ሀሳብ ይሁንታ ሳያገኝ ቀርቷል፡፡
ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝደንት በመሆኗ ያንን ለማስቀጠል በስራ አስፈጻሚነት ትካተት የሚለው ሀሳብ ለጉባኤው ቀርቧል፡፡
ጉባኤው ባደረገው ክርክርም በተለይ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ ከጸደቀ በኋላ ለምን ጉዳዩ ተነሳ የሚል የመከራከሪያ ሃሳብ ተነስቷል፡፡
መመሪያው ካልተሻሻለ በስተቀር በምንመልኩ ነው የምናካትተው የሚል ሃሳብም ጉባኤተኛው ተወያይቷል፡፡
በአፍሪካ ያለን የስፖርት አመራርን ለማብዛት በስራ አስፈጻሚ ትቀጥል የሚል ሀሳብም ቀርቧል፡፡
በመጨረሻም ጉዳዩ እልባት ሳያገኝ ድምጽ ሳይሰጥበት ተዘግቷል፡፡
በሃብታሙ ካሴ