በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አሸናፊ ለሆኑ አትሌቶች ሽልማት ተሰጠ

26 Days Ago 256
በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አሸናፊ ለሆኑ አትሌቶች ሽልማት ተሰጠ

በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር ሩጫ አሸናፊ ለሆኑት አትሌቶች ሽልማት የመስጠት ስነ-ስርዓት ተካሂዷል፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትር ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሴቶች 10 ኪሎ ሜትር ሩጫ 1ኛ ለወጣችው አትሌት አሳየች አይቸው ሽልማት አበርክተዋል፡፡

በውድድሩ ሁለተኛ የወጣችው አትሌት የኔዋ ንብረት ከሶፊ ማልት ተወካይ ሽልማቷን የተቀበለች ሲሆን፣ አትሌት ገብረ እግዚአብሔር ገብረ ማርያም ሦስተኛ ለወጣችው አትሌት ቦሰና ሙላቱ ሽልማቱን አበርክቷል፡፡ 

እንዲሁም በወንዶች 1ኛ የወጣው አትሌት ቢኒያም መሐሪ ሽልማቱን ከቱሪዝም ሚኒስትር ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ እጅ ተቀብሏል፡፡

2ኛ የወጣው አትሌት አዲሱ ነጋሽ ከሶፊ ማልት ተወካይ ሽልማቱን የተቀበለ ሲሆን፣ አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 3ኛ ለወጣው አትሌት ይስማው ድሉ ሽልማቱን አበርክቷል፡፡

በሁለቱም ጾታዎች 1ኛ ለወጡት አትሌቶች 250 ሺህ ብር፣ 2ኛ ለወጡት 150 ሺህ ብር እንዲሁም 3ኛ ሆነው ለጨረሱት 100 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን፣ ኢትዮ ቴሌኮም እና ሶፊ ማልት ልዩ ሽልማት ማዘጋጀታቸው ታውቋል፡፡

📸EBC DOTSTREAM

#GreatEthiopianRun #ኢትዮጵያ #EBC #etv #Ethiopia #EBCDOTSTREAM #ታላቁ_ሩጫ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top