አዲስ የተሾሙት ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ማን ናቸው?

8 Days Ago 461
አዲስ የተሾሙት ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ማን ናቸው?
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የተወለዱት በደባርቅ ሰሜን ጎንደር ነው፡፡
 
የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት አግኝተዋል።
እንግሊዝ ከሚገኘው ላንክስተር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በዓለም አቀፍ ግንኙነት እና በስትራቴጂ ጥናት ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ወስደዋል።
 
በተለያዩ ሀገራት አጫጭር የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ፖለቲካል ሳይንስ ሥልጠናዎችን እና ኮርሶችን ወስደዋል።
 
ፕሬዚዳንት ታዬ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ መምሪያ የሥራ ክፍል፣ የምዕራብ አውሮፓ ዋና ክፍል ኃላፊ፣ የኢንፎርሜሽን ተጠባባቂ ዳይሬክተር፣ ስቶክሆልም የኢፌዲሪ ኤምባሲ በአማካሪነት፣ በዋሽንግተን የኢፌዲሪ ኤምባሲ በአማካሪነት በሎስአንጀለስ ቆንስል ጀነራል፣ በ1998 ዓ.ም ባለሙሉሥልጣን አምባሳደርነት ተሹመዋል።
 
በሎስአንጀለስ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት ማዕረግ የቆንስላ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ በአውሮፓ እና አሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል፣ በ2008 ዓ.ም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው አገልግለዋል።
 
በግብፅ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ተጠሪ ሆነውም ሀገራቸውን አገልግለዋል።
 
ፕሬዚዳንት ታዬ ወደሀገር ቤት ተመልሰው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ሰረተዋል።
 
ኢትዮጵያን በመወከል የ74ኛው የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የተባበሩት መንግስታት ዩኒሴፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምክትል ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡
 
ባለፉት 4 አስርት ዓመታት ሀገራቸውን እና ህዝባቸውን በታላቅ ቅንነት፣ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት እና ታማኝነት ያገለገሉ ሲሆን ለዚህም የረጅም ዘመን የመንግሥት ሰራተኛ አገልግሎት የክብር የምስክር ወረቀት አግኝተዋል፡፡
 
ፕሬዚዳንት ታዬ እስከዛሬዋ ቀን ድረስ ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሀገራቸውን አገልግለዋል።
 
በዛሬው እለት ደግሞ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾመዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top