ኢትዮጵያ እየተገበረቻቸው ያሉ በርካታ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ጥያቄዋ በፍጥነት መልስ እንዲያገኝ ያግዛል፡- ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር)

31 Days Ago 270
ኢትዮጵያ እየተገበረቻቸው ያሉ በርካታ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ጥያቄዋ በፍጥነት መልስ እንዲያገኝ ያግዛል፡- ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር)
መንግስት በአሁኑ ወቅት እየተገበራቸው ያሉ በርካታ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ጥያቄዋ በፍጥነት መልስ እንዲያገኝ እንደሚያግዝ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡
 
ሚኒስትሩ ከዓለም የንግድ ድርጅት አክሴሽን ዲቪዥን ዋና ዳይሬክተር ማይካ ኦሺካዋ ጋር በአገሪቱ የዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት የድርደር ሂደት ላይ ውይይት አካሄደዋል፡፡
 
ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ጥያቄ ካቀረበች ረዥም ጊዜ ያስቆጠረች ሲሆን የኢኮኖሚ ማሻሻያው የድርድር ሂደቱን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እንደሚያግዝ ሚኒስትሩገልፀዋል፡፡
 
በቀጣይ ለሚካሄደው 5ኛው የስራ ቡድን ስብሰባ ላይ የሚቀርቡ ሰነዶች ወደ ተግባር የገቡ በርካታ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ያካተተ እንዲሆን ከድርጅቱ ባለሙያዎች ጋር ሰነድ በመከለስ ሂደት ላይ እንደሚገኙ አብራረተዋል፡፡
 
የዓለም የንግድ ድርጅት አክሴሽን ዲቪዥን ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ የአባልነት ጥያቄን ካጓተቱ ምክንያቶች መካከል በቅርቡ ተግባራዊ መሆን የጀመረው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ማሻሻያው የድርድር ሂደቱን እንደሚያፋጥን እምነታቸውን መግለጻቸውን የሚስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አያይዘው የዓለም ንግድ ድርጅት ያለ ኢትዮጵያ ተሳትፎ ሙሉ አይሆንም ያሉት ዳይሬክተሯ ድርድሩን በአጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ ድርጅቱ ቴክኒካል ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚሰጥል ተናግረዋል።
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top