ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የክህሎት ተቋም አባል ሀገር ሆነች

5 Mons Ago 545
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የክህሎት ተቋም አባል ሀገር ሆነች
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የክህሎት ተቋም "ወርልድ ስኪል" አባል ሀገር ሆና መመዝገቧን የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ገለጸ።
 
የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የክህሎት ተቋም አባል ሀገር መሆኗን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ሰጥተዋል።
 
በማብራሪያቸውም መንግስት ክህሎት ያላቸውና አምራች ዜጎችን ለመፍጠር በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
 
በዚህም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፉን ይበልጥ በማዘመን ውጤታማነቱን የሚያረጋግጡ የሪፎርም ስራዎችን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።
 
ሪፎርሙም የዜጎችን የክህሎት ልማት ስራዎች ማዘመንና ተደራሽነትን ማስፋት ላይ ትኩረቱን እንደሚያደርግ ገልፀዋል።
 
በተጨማሪም ዘርፉ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ያለውን አስተዋጽኦ በማሳደግ ረገድ ጉልህ ድርሻ እንዲኖረው ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
 
በዚህ ረገድ ብቁና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ዜጎችን መፍጠር ዋነኛ ዓላማ ተደርጎ እየተተገበረ ይገኛል ብለዋል።
በመሆኑም በክህሎት ልማት ላይ የሚሰራው ዓለም አቀፍ የክህሎት ተቋም ኢትዮጵያን 88ኛ አባል ሀገር አድርጎ መመዝገቡን ተናግረዋል።
 
ይህም በአባል ሀገራቱ መካከል የሚደረጉ የክህሎት ውድድሮች ላይ ለመሳተፍ እና አቅምን ለማጎልበት የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።
 
ከዚህም ባሻገር ዘለቂ የሆነ የኢንዱስትሪ ትስስርና ቅንጅታዊ አሰራርን ለማጎልበት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
 
በመሆኑም በመጪው መስከረም ወር በፈረንሳይ ሊዮን ከተማ ተቋሙ በሚያዘጋጀው 47ኛው ዓለም አቀፍ የክህሎት ውድድር ላይ በዘርፉ ብቁ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች እንደሚሳተፉ አረጋግጠዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top