የፒያሳ እና የአራት ኪሎ መስመር ስራ በተያዘው የሦስት ወር መርሐ-ግብር ማጠናቀቃችንን ስገልፅ ደስታ ይሰማኛል፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

1 Mon Ago
የፒያሳ እና የአራት ኪሎ መስመር ስራ በተያዘው የሦስት ወር መርሐ-ግብር ማጠናቀቃችንን ስገልፅ ደስታ ይሰማኛል፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የፒያሳ እና የአራት ኪሎ መስመር ስራ በተያዘው የሦስት ወር መርሐ-ግብር ማጠናቀቃችንን ስገልፅ ደስታ ይሰማኛል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ፤ የቀደሙትን የኮሪደር ልማት ስራዎች ግምገማ ስናጠናቅቅ ቀጣዩን ግምገማችንን በስራው ስፍራ ተገኝተን እንደምናካሂድ ቃል ገብተን ነበር ብለዋል።
 
በቀጣይ ስራ ሀብት ቁጠባ ቀዳሚ ትኩረት ሆኖ በቀሪ ኮሪደሮች ስራዎቻችን ፈጣን እና ፈጠራ መር ልንሆን ይገባል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
 
ጥራትን ማስጠበቅ እና ለዜጎቻችን ሁሉ የተመቸ ከባቢን መፍጠር ቅድሚያ የምንሰጣቸው ተግባራት ናቸው ሲሉም ገልጸዋል።
 
ይህ ፕሮጀክት የሚራመደው በብዙሃን ትብብር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከጅማሮው በስራችን ባገኘነው በጎፈቃድ ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል።
 
ይህም በዕቅድ እና አፈፃፀም ላይ የታየውን ጥረታችንን እና መልካም ፈቃዳችንን የመጠነ ሆኖ ታይቷል ነው ያሉት።
 
በዚህ ከተማችንን ለተሻለ ለውጥ ለማብቃት በተደከመበት ታላቅ ስራ ሂደት ውስጥ በዜጎቻችን ላይ ፈጥረነው ሊሆን ለሚችል አለመመቸት ይቅርታ እንጠይቃለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።
 
አክለውም፤ ኢትዮጵያችን እንድትለወጥ በፅናት እንደምንሰራ በዚህ የኮሪደር ልማት ስራ ሂደትም ያሉ የዲዛይን እና የጥራት ክፍተቶችም ካሉ ማስተካከል እንደምንቀጥል እንድትተማመኑ ለመግለፅ እፈልጋለሁ ብለዋል።
 
በግሉ ዘርፍ ያሉ አጋሮቻችንን ጨምሮ ትናንት ምሽት በጎዳናዎች ፍቅራችሁን ለገለፃችሁልን፤ በአጠቃላይም በዚህ ስራ ለተሳተፋችሁ ሁሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top