በቤንች ሸኮ ዞን አንዲት እናት በአንድ ጊዜ 4 ልጆችን በሰላም ተገላገለች

10 Mons Ago 679
በቤንች ሸኮ ዞን አንዲት እናት በአንድ ጊዜ 4 ልጆችን በሰላም ተገላገለች

በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል አንዲት እናት በአንድ ጊዜ 4 ልጆችን በሰላም መገላገሏ ተገለጸ።

በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ ልዩ መጠሪያው ኮሰኮል ነዋሪ የሆነችው ይቺ እናት ሦስት ወንድ እና አንድ ሴት ልጆችን ነው በሰላም የተገላገለችው።

ህጻናቱ በሆስፒታሉ የእናቶችና ጨቅላ ህጻናት ህክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን እያንዳንዳቸው ከ1.3 እስከ 1.7 ኪሎግራም ክብደት እንዳላቸው ከዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top