በወዳጅነት ጨዋታ ኢትዮጵያ ኡጋንዳን 1-0 አሸነፈች

10 Mons Ago 934
በወዳጅነት ጨዋታ ኢትዮጵያ ኡጋንዳን 1-0 አሸነፈች

በድሬዳዋ ከተማ ዓለም አቀፍ ስታዲየም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከኡጋንዳ አቻው ጋር ያደረጉት አለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታ በዋሊያዎቹ 1 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቅቋል፡፡

በጫዋታው ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ ቢንያም አይተን ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አስቆጥሯል፡፡

ይህ የወዳጅነት ጨዋታ የድሬዳዋ ከተማ ስታዲየም የፊፋ እና ካፍ መስፈርቶችን በማሟላት አለም አቀፍ ጨዋታዎችን ለማስተናገድ የሚያስችለውን ደረጃ ካገኘ በኋላ የተደረገ የመጀመሪያ ጨዋታ ነው፡፡

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ የስቴዲየሙን የማስፋፊያ እና እድሳት ስራዎችን ያከናወነ ሲሆን በዛሬው እለትም የስታዲየሙ እድሳት ተጠናቆ መመረቁን ከከተማ አስተዳደሩ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top