ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ የልዑካን ቡድን አሸኛኘት ተደረገ

1 Mon Ago
ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ የልዑካን ቡድን አሸኛኘት ተደረገ

በቱኒዚያ ለሚካሄደው የአፍሪካ አገር አቋራጭ ውድድር እና በእንግሊዝ ግላስኮው ለሚደረገው 19ኛው የአለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ለሚወክለው ልዑክ ቡድን አሸኛኘት ተደረገለት።

ለልዑክ ቡድኑ አሸኛኘት የተደረገለት ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት በስለሺ ሆቴል ነው።

ግላስኮ ላይ በቀጣይ ሳምንት በሚደረገው ውድድር ኢትዮጵያ በ1500 እና በ3000 ሜትር በሁለቱም ፆታ የምትሳተፍ ሲሆን፤ በ800 ሜትር ደግሞ በሴቶች ትወከላለች።

ቱኒዚያ ላይ በሚደረገው እና የፊታችን እሁድ በሚጀምረው 6ኛው የአፍሪካ አገር አቋራጭ ውድድር ኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች በሴቶች 6 ኪ.ሜ እና በወንዶች 8 ኪ.ሜ ውድድር ትሳተፋለች፡፡

በሌላ በኩል በአዋቂዎች 10 ኪ.ሜ ውድድሮች ሲደረጉ ኢትዮጵያ በ14 ሴቶች እና 14 ወንዶች የምትሳተፍ ይሆናል።

በምህረት ተስፋየ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top