የአማራ ክልል መንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ስልጠና ለገቡ ሰልጣኞች አቀባበል ተደረገ

8 Mons Ago 843
የአማራ ክልል መንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ስልጠና ለገቡ ሰልጣኞች አቀባበል ተደረገ
የአማራ ክልል መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ስልጠና ለገቡ ሰልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ተደረገላቸው።
 
በስነ-ስርዓቱ ላይ የክልሉ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው፣ የምስራቅ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሃመድ ተሰማ ፣ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሀኑ በቀለ እንዲሁም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደስየ ደጀን ተገኝተዋል።
 
በስነስርዓቱ ላይ አቶ ደሳለኝ ጣሰው፤ የተሃድሶ ሰልጣኞች ውግንናችሁን ለሕገ-መንግስቱ እና ለህዝብ መሆኑን አምናችሁና ተቀብላችሁ ስለመጣችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
 
ሌተናል ጄኔራል ብርሀኑ በቀለ በበኩላቸው፤ ሀገርና ህዝብን ለመካስ ዳግመኛ ያገኛችሁትን ዕድል በአግባቡ በመጠቀም ለሀገራችሁ ዘብ መቆም አለባችሁ ሲሉ አሳስበዋል።
 
"ይሄን የሰላም ጥሪ ተቀብላችሁ ወደ ሰላም በመምጣታችሁ ጀግኖች ናችሁ" ያሉት ሌተናል ጀኔራል መሀመድ ተሰማ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚጥሩ ኃይሎችን ለመታገል ዳግመኛ እድል አግኝታችኋልና በአግባቡ ልትጠቀሙበት ይገባል ብለዋል።
 
የተሃድሶ ሰልጣኞች የክልሉን ህዝብ እንዲሁም ሀገራቸውን ለመጠበቅ ቃል መግባታቸውንም የአማራ ክልል ፖሊስ መረጃ ያመለክታል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top