"ፀሐይ" ወደ ኢትዮጵያ መመለሷ ለቀጣዩ ትውልድ ትልቅ መነቃቃትን የሚፈጥር ነው - የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን

2 Mons Ago
"ፀሐይ" ወደ ኢትዮጵያ መመለሷ ለቀጣዩ ትውልድ ትልቅ መነቃቃትን የሚፈጥር ነው -  የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን

 

የ"ፀሐይ" አውሮፕላን መመለስ ለቀጣዩ ትውልድ ትልቅ መነቃቃትን የሚፈጥር እና ለተቋሙም ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ገለጸ፡፡

ባለስልጣኑ “ፀሐይ” አውሮፕላን ወደ ኢትዮጵያ መመለስን አስመልክቶ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፏል፡፡

በመልዕክቱም፤ “ፀሐይ” አውሮፕላን በሀገራችን የአቪዬሽን ታሪክ ጉልህ ሚና ያላትና ከ87 ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ምድር ተሰርታ የተሳካ የሙከራ በረራ ለማድረግ የቻለች መሆኗን ገልጿል፡፡

"ፀሐይ" በዳግም የጣሊያን ወረራ ወቅት ወደ ጣልያን ተወስዳ በሙዚዬም ለዓመታት ተቀምጣ እንደነበረች ያወሳው ባለስልጣኑ፤ አውሮፕላን ወደ ኢትዮጵያ በመመለሷም የተሰማውን ደስታ ገልጿል፡፡

"ፀሐይ" የሀገራችን የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ፈር ቀዳጅ ተደርጋ ትቆጠራለች ሲል የገለጸው ባለስልጣኑ፤ ኢንዱስትሪውን በራሳችን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ውጤቶች ለመተካት እየተደረገ ላለው ጥረት የሞራል ስንቅ እንደምትሆን አመልክቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "ፀሐይ" እንድትመለስ ላደረጉት ጥረትም የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ምስጋና አቅርቧል፡፡  


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top