የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ተወካዮች ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶችን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስረከቡ

3 ወር በፊት
የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ተወካዮች ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶችን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስረከቡ

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ተወካዮች በእጃቸው የሚገኙ ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶችን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስረክበዋል።

ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶች በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እንዲቀመጡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ ነው የክልሉ ተወካዮች ቅርሶቹን ለከተማ አስተዳደሩ ያስረከቡት።

የከንቲባ ጽህፈት ቤት እና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቁ፤ የከተማ አስተዳደሩ ያቀረበውን ጥሪ በመቀበል የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ከተለያዩ ዞኖች ያሰባሰባቸውን ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶችን ስላበረከቱ በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ሌሎችም የነዚህን አርዓያ በመከተል፤ ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶች ትውልድ እንዲማርባቸው በዓድዋ ድል መታሰቢያ እንዲቀመጡ በእጃቸው የሚገኙ ቅርሶችን እንዲያበረክቱ ጥሪ ማቅረባቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top