የአርብቶ አደሩ አካባቢ ያሉ ዕድሎችን እና ፈተናዎች የተመለከተ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው

2 Mons Ago
የአርብቶ አደሩ አካባቢ ያሉ ዕድሎችን እና ፈተናዎች የተመለከተ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው
የአርብቶ አደሩ አካባቢ ያሉ ዕድሎችን እና ፈተናዎችን የተመለከተ የፓናል ውይይት በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።
 
በውይይቱ የተለያዩ ጥናታ ጽሁፎች ቀርበው መፍትሄ አመላካች የሆኑ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
 
በአውደ ርዕዩ ላይ የአርብቶ አደሩ አካባቢዎች ላይ ያሉ ሰፋፊ መሬቶች እና የእንስሳት ሃብቶች መኖራቸው ተገልጿል።
 
እነዚህን የልማት ዕድሎች አሟጦ ለመጠቀም የሚያስችሉ ሁኔታዎች በሰፊው መፈጠር አለባቸው የሚሉ ሀሳቦች ከተሳታፊ አርብቶ አደሮች እና ባለድርሻ አካላት ተነስቷል።
 
በአርብቶ አደሩ አካባቢ ያሉ የእንስሳት ሀብቶች በኮንትሮባንድ ከሀገር እንደሚወጡ የተገለጸ ሲሆን፤ ችግሮቹን ለመቅረፍ መሠረተ ልማቶችን በመዘርጋት እና የገበያ ዕድሎችን በመፍጠር የአርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት ማሳደግ ተገቢ መሆኑም ተገልጿል።
 
የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ በአርብቶ አደሩ አካባቢ ያሉ መሬቶችን ለግብርና እና ለሌሎች ልማቶች ለማዋል እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል።
 
ከክልሉ የሽንሌ ዞን የመስኖ ውኃ አማራጮችን በመጠቀም ግብርና ላይ በስፋት መሥራት፣ ለእንስሳቶች የመኖ ሳር የማልማት እንዲሁም የአርብቶ አደሩን ህልውና የማረጋገጥ ስራ በስፋት መጀመሩንም ተናግረዋል።
 
በሀገር ውስጥ አርብቶ አደሩ የእንስሳት ተዋጽኦችን ለገበያ ማቅረብ የሚችልበት ዕድል መኖር እንዳለበትም የተጠቀሰ ሲሆን፤ የአርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የፋይናንስ አካታችነት ላይ በትኩረት መሠራት አለበትም ተብሏል።
 
በውይይት መድረኩ ላይ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ፣የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ ኦመር፣የዓለም ባንክ ምክትል ፕሬዚደንት ኦስማኔ ዲዮኒ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
 
በመሃመድ ፊጣሞ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top