ኢዜአ ያስገነባው ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ተመረቀ

2 Mons Ago
ኢዜአ ያስገነባው ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ተመረቀ

አንጋፋው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት(ኢዜአ) ያስገነባውን ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ የምረቃ ሥነ-ስርዓት ተካሄደ።

በምርቃት ሥነ-ስርዓቱ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሚዲያ አመራሮችና ሌሎችም እንግዶች ተገኝተዋል።

የሚዲያ ኮምፕሌክሱ ዘመኑ የደረሰበትን የሚዲያ ቴክኖሎጂ ያሟላ ሲሆን ሦስት የቴሌቪዥንና አራት የሬዲዮ ዘመናዊ ስቱዲዮዎችን አካቷል።

በተጨማሪም ለቢሮ አገልግሎት የሚሆኑ በርካታ ክፍሎች፣ የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣ ቤተ-መጽሀፍት፣ የመዝናኛ ማዕከልና ዘመናዊ ጂምናዝየም አሉት።

ከተመሠረተ 81 ዓመታትን የተሻገረው አንጋፋው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ብሔራዊ መግባባት የመፍጠርና የሀገር ገፅታ ግንባታ ተልዕኮውን ለማሳካት ዜና እና ዜና ነክ መረጃዎችን ተደራሽ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ተቋሙ ያስገነባው ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስም በዛሬው እለት በደማቅ ሥነ ስርአት ተመርቋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top