በደቡብ ወሎ ዞን ከ77 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች ተመረቁ

2 Mons Ago
በደቡብ ወሎ ዞን ከ77 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች ተመረቁ

በደቡብ ወሎ ዞን ሐይቅ ከተማ አስተዳደር የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከ77 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል

በዛሬው ዕለት ለምረቃ ከበቁት ፕሮጀክቶች መካከል በዓለም ባንክ በ56 ሚሊዮን ብር ወጭ የተገነባው የከተማ አስተዳደሩ ቢሮ እና በአንድ ባለሐብት በ21 ሚሊዮን ብር የተገነባው የነዳጅ ማደያ ይገኙበታል።  

በዚህ ወቅት የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መሰተዳድር አብዱ ሁሴን፤ ለምረቃ የበቁት ፕሮጀክቶች በአጭር ጊዜ በጥራት መገንባታቸው ብልጽግና ፓርቲ ያስቀመጠው አቅጣጫ ተግባራዊነት ማሳያ ናቸው ብለዋል።

የቢሮ ግንባታው የመንግስት ሠራተኞች የሥራ ተነሳሽነትን በመጨመር የሕዝቡን የአገልግሎት እርካታ ለመፍጠር ሊጠቀሙበት ይገባል ብለዋል።

የሐይቅ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር መሐመድ በ56 ሚሊየን ብር የተገነባው የመንግስት ቢሮ በአንድ ዓመት ተኩል መጠናቀቁን ገልጸዋል።

የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አሊ መኮንን፤ ሐይቅ ከተማ በጦርነቱ ጉዳት ከደረሰባቸው አካባቢዎች አንዷ መሆኗን ገልጸው፤ መንግስት መልሶ ለመገንባት በገባው ቃል መረሰት ዛሬ የተመረቀውን ህንጻና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን መሥራት ተችሏል ብለዋል።  

በምረቃው ላይ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋየ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ክላስተር አስተባባሪና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አህመዲን መሐመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን የክልሉ ከሙዩኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top