“ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የምግብ ሉአላዊነት በማረጋገጥ በኩል ታላቅ ውጤት አስመዝግበዋል“ - የተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጀት ዳይሬክተር

7 Mons Ago 598
“ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የምግብ ሉአላዊነት በማረጋገጥ በኩል ታላቅ ውጤት አስመዝግበዋል“ - የተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጀት ዳይሬክተር

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የምግብ ሉአላዊነት በማረጋገጥ በኩል ታላቅ ውጤት አስመዝግበዋል ሲሉ በተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጀነራል ገርድ ሙለር ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት በሮም ጣልያን በተሰናዳ ክብረ በዓል የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያ ተሸልመዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት ያስተላለፉት የተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጀት ዳይሬክተር ጀነራል ገርድ ሙለር፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የምግብ ሉአላዊነት መረጋገጥ በኩል ታላቅ ውጤት ማስመዝገብ መቻላቸውን ተናግረዋል።

ባለፉት ጥቂት አመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በምግብ ምርት ረገድ ከፍተኛ ውጤት መገኘቱን የገለጹት ዳይሬክተሩ በእጥፍ ያደገው የስንዴ ምርት ለዚህ ተጠቃሸ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በምግብ እህል ምርት እራሷን ለመቻል በምታደርገው ጥረትም ድርጅታቸው ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠንካራ አመራር ሰጪነት በተገኘው የግብርና ምርት እድገት ኢትዮጵያ ለሌሎች የአፍሪካ ሃገራትም ሆነ ለሌላው ዓለም በሞዴልነት ልትጠቀስ እንደምትችል አሳይታለች ብለዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top