ተጨማሪ ፍተሻዎቹ እንዲደረጉ የተወሰነው የአሜሪካ ፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር 737 MAX አውሮፕላኖችን ከበረራ ካገደ በኋላ ነው።
የቦይንግ ንግድ አይሮፕላኖች ፕሬዚዳንት ስታን ዲል ለዓለም አቀፉ አውሮፕላን አምራቾች በጻፉት ደብዳቤ፣ የበሮቹን ብሎኖች ለኩባንያው የሚያቀርበው ስፒሪት ኤሮሲስተምስ የተባለ አቅራቢ ቡድን እንደሆነ ገልጸዋል።
እነዚህ የስፕሪት ምርቶች በአሜሪካ ግዛቶች ወደሚገኙ የቦይንግ ምርት ተቋማት ከመምጣታቸው በፊት ጥራታቸውን የሚያረጋግጥ ቡድን መቋቋሙን ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል።
ድርጅቱ አውሮፕላኖቹ ወደ በረራ መመለስ አለመመለሳቸውን የሚያሳውቀው የ40 አውሮፕላኖች የምርመራ ውጤት ከተመለከቱ በኋላ እንደሆነ የአሜሪካ ፌዴራል አቪዬሽን አስተዳደር (FAA) መግለጹን አልጀዚራ ዘግቧል።