100 ቀናትን ያስቆጠረው የእስራኤል-ሐማስ አውዳሚ ጦርነት

3 Mons Ago
100 ቀናትን ያስቆጠረው የእስራኤል-ሐማስ አውዳሚ ጦርነት

100 ቀናትን ያስቆጠረው የእስራኤል-ሐማስ ጦርነት በሁለቱ ወገኖች መካከል ከተደረጉት ጦርነቶች ሁሉ ረጅም፣ ይበልጥ ደም አፋሳሽ እና አውዳሚው ነውም ተብሏል።

ጦርነቱ የተቀሰቀሰው እ.ኤ.አ ጥቅምት 7 ሐማስ በደቡባዊ እስራኤል ድንገተኛ ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ ነበር።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስራኤል የጋዛ ሰርጥን በአየር እና በእግረኛ ጦር ያለረፍት በመደብደብ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ ውድመት አድርሳለች።

ጥቃቱ ከጋዛ ነዋሪዎች ውስጥ 85 በመቶ የሚሆኑትን ከማፈናቀሉ በተጨማሪ፤ በሺዎች የሚቆጠሩትን ለሕልፈት ዳርጓል።

ይህ ብቻ አይደለም፥ በጋዛ ከሚገኙ ሆስፒታሎች ከግማሽ በላይ በሚደርሱት የጤና አገልግሎት ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጥ አድርጓል።

ከዚህም አልፎ ጥቃቱ በጋዛ ረሃብ እንዲንሰራፋ ማድረጉን የመንግሥታቱ ድርጅት ተቆጣጣሪዎችን ጠቅሶ አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል።

የእስራኤል ወታደራዊ ኃይል አሁን ላይ በሰሜናዊ ጋዛ የሚያካሂደውን ኦፕሬሽን ስለመቀነሱ ቢገልፅም፤ የሐማስ መሪዎች ተደብቀውበታል በሚለው ደቡባዊ ጋዛ ጥቃቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።

የእስራኤል-ሐማስ ጦርነትን በተመለከተ ከፍልስጥኤም የጤና ሚኒስቴር እና ከእስራኤል ባለስልጣናት እንዲሁም ከዓለም አቀፍ ታዛቢዎች እና የእርዳታ ቡድኖች በተገኘ ቁጥራዊ መረጃ መሠረት፦

 • ጋዛ ውስጥ የተገደሉ ፍልስጥኤማውያን ቁጥር - 23,843
 • እስራኤል ውስጥ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር - ከ1,200 በላይ
 • ዌስት ባንክ ውስጥ የተገደሉ ፍልስጥኤማውያን ቁጥር - 347
 • በጋዛ የተገደሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰራተኞች - 148
 • በጋዛ የተገደሉ የጤና ሰራተኞች - ቢያንስ 337
 • በጋዛ የተገደሉ ጋዜጠኞች - 82
 • በእስራኤል የተገደሉ የሐማስ ተዋጊዎች - 8,000
 • በጋዛ የተገደሉ የእስራኤል እግረኛ ወታደሮች - 187
 • የወደሙ የጋዛ ሕንፃዎች - ከ45 እስከ 56 በመቶ
 • ጋዛ ውስጥ ከነበሩ 36 ሆስፒታሎች በከፊል ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ - 15
 • ለአስከፊ ረሃብ የተጋለጡ ፍልስጥኤማውያን - 26 በመቶ (576,600)
 • በጋዛ የተጎዱ የትምህርት ቤት ሕንፃዎች - ከ69 በመቶ በላይ
 • በጋዛ ወደፍርስራሽነት የተቀየሩ ቤተ እምነቶች - 142 መስጊዶች እና 3 አቢያተ ክርስቲያን
 • በጋዛ የተቃጠሉ አንቡላንሶች - 121
 • ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ተማሪዎች - 625,000 (100 በመቶ)
 • ከጋዛ የተፈናቀሉ ፍልስጥኤማውያን ቁጥር - 85 በመቶ (1.9 ሚሊዮን)
 • የተፈናቀሉ እስራኤላውያን ቁጥር - 2.6 በመቶ (249,263)
 • በሐማስ ታግተው የነበሩ ሰዎች ቁጥር - 253
 • የተለቀቁ ታጋቾች ቁጥር - 121
 • ያልተለቀቁ ታጋቾች ቁጥር - 132
 • በእገታ ላይ ሆነው የተገደሉ ወይም የሞቱ ታጋቾች ቁጥር - 33
 • የተለቀቁ ፍልስጥኤማውያን እስረኞች ቁጥር - 240

በናርዶስ አዳነ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top